Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለ 8 ነጥብ 8 ሚሊየን ሴቶች የማሕጸን በር ጫፍ ካንሰር ክትባት ይሰጣል – ጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 22 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ 8 ነጥብ 8 ሚሊየን ዜጎች የማሕጸን በር ጫፍ ካንሰር ክትባት በዘመቻ ለመሥጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በጤና ሚኒስቴር የክትባት ክፍል አማካሪ አቶ መንግስቱ ቦጋለ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትጋራ ባደረጉት ቆይታ፥ ክትባቱ ዕድሜያቸው ከ9 እስከ 14 ለሆኑ 8 ነጥብ 8 ሚሊየን ሴቶች ይሠጣል ።

ከዚህ ቀደም ዕድሜያቸው 14 ዓመት ለሆኑ ሴቶች ብቻ ክትባቱ ሲሰጥ የቆየ ሲሆን አሁን ላይ በቂ ግብዓት በመኖሩ ከ9 እስከ 14 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሴቶች እንዲወስዱ መወሰኑንም አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም ሁለት ዶዝ የነበረው ክትባት ከዚህ በኋላ አንድ ዶዝ ብቻ እንደሚሠጥም ነው የጠቆሙት።

ከዚህ በኋላ ክትባቱ ዕድሜያቸው 9 ዓመት ለሆኑ ሴቶች ብቻ በመደበኛነት እንደሚሰጥም አስገንዝበዋል።

ክትባቱ በነጻ ይሰጣል ያሉት አማካሪው ጥር ወር መጨረሻ ላይ ለመጀመር ዕቅድ መያዙንም ነው የተናገሩት።

ክትባቱም በሀገር ዓቀፍ ደረጃ በትምህርት ቤቶች ፣ በደርሶ መልስ ጣቢያዎች እና በጤና ድርጅቶች እንደሚሰጥ አቶ መንግስቱ ገልጸዋል።

የማሕጸን በር ጫፍ ካንሰር ያልተነገረለት በሽታ ነው ያሉት አቶ መንግስቱ በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ5 ሺህ 300 በላይ ሴቶች በዚሁ በሽታ ሕይወታቸው እያለፈ ነው ብለዋል።

በመሳፍንት እያዩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version