ዓለምአቀፋዊ ዜና

ተለያዩ ሀገራት አዲስ ዓመታቸውን 2024 ተቀበሉ

By Melaku Gedif

January 01, 2024

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 22 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎርጎሮሳውያን የዘመን አቆጣጠር ቀመር የሚጠቀሙ ሀገራት አዲሱን ዓመት 2024  ተቀብለዋል።

ሀገራቱ በዋና ከተሞቻቸው በተለያዩ የርችት ትርዒቶች እና ደማቅ ሥነ-ሥርዓቶች ነው አዲሱን ዓመት የተቀበሉት።

አውስትራሊያ እና ኒውዝላንድ 2024ን ቀድመው የተቀበሉ ሀገራት መሆናቸውን ሬውተርስ ዘግቧል።

ሩሲያ፣ ህንድ፣ ጃፓን፣ እንግሊዝ ፣ደቡብ ኮሪያ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ እና ሌሎች ሀገራትም የጎርጎሮሳውያኑን 2024 አዲስ ዓመት ተቀብለዋል።

በሺህዎች የሚቆጠሩ የየሀገራቱ ዜጎችም አዲሱን ዓመት ለመቀበል በዋና ከተማዎች አደባባዮችና ማማዎች ላይ የተዘጋጁ የርችት ሥነ-ሥርዓቶችን ታድመዋል።