ስፓርት

2023 ለሴቶች 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር ታሪካዊ ዓመት ነበር ተባለ

By Shambel Mihret

December 31, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንጆቹ 2023 ለሴቶች 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር የተለየ ዓመት እና ታሪካዊ እንደነበረ የዓለም አትሌቲክስ ገለጸ።

በዓመቱ የርቀቱ ክብረ ወሰን ሁለት መሰበሩን ጠቅሷል።

ከዚህ በተጨማሪም የርቀቱ የምንጊዜም 10 ፈጣን ሰዓት መካከል ስድስቱ በዚህ ዓመት የተመዘገበ መሆኑን የዓለም አትሌቲክስ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ አመልክቷል።

የርቀቱን የዓለም ክብረ ወሰን በአሜሪካ ኢውጅን በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ 14 ደቂቃ ከ00 ሴኮንድ ከ21 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት በእጇ ማስገባቷ ይታወቃል።