አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 21 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎብኚዎች መዳረሻ የሆነችው የጣሊያኗ ቬኒስ ከተማ በቡድን የሚደረግ ጉብኝት እና ድምጽ ማጉያዎችን ልታግድ መሆኑ ተሰማ።
የከተማዋ አስተዳደር ውሳኔ ከ25 በላይ ሆነው የሚመጡ ጎብኚዎችን የማያስተናግድ ሲሆን፥ አሰራሩ ከፈረንጆቹ ሰኔ ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።
ውሳኔው ከተማዋ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ጎብኚዎች የሚደርስባትን መጨናነቅ እና ጫና ለመቀነስ ያለመ መሆኑን ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል።
ከዚህ ባለፈም ድምጽ ማጉያዎች የሚያወጡት ድምጽ “ግርታን የሚፈጥሩና የከተማዋን ጸጥታ የሚረብሹ በመሆናቸው” ሳቢያ ጥቅም ላይ ማዋል እንደማይቻልም ነው የተገለጸው።
ቬኒስ በአውሮፓ በከፍተኛ ደረጃ ከሚጎበኙ ቀዳሚ የቱሪዝም መዳረሻዎች መካከል አንዷ መሆኗ ይነገራል።
አነስተኛዋ ከተማ በየአመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ጎብኚዎችን እንደምታስተናግድ መረጃዎች ያመላክታሉ።
የከተማዋ አስተዳደር ከዚህ ቀደም የጎብኚዎችን ቁጥር ለመቆጣጠር ከ14 ዓመት በላይ የሆናቸው ጎብኚዎች ወደ ከተማዋ ለመግባት የ5 ዩሮ ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚያስገድድ ሕግ አውጥቶ ነበር።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!