ቢዝነስ

ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ ለማቅረብ መዘጋጀታቸውን የሌማት ትሩፋት ተጠቃሚዎች ገለጹ

By ዮሐንስ ደርበው

December 30, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መጪውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ እንቁላል፣ ዶሮና የወተት ተዋፅዖ በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ ለማቅረብ መዘጋጀታቸውን በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የሌማት ትሩፋት ተጠቃሚዎች ገለጹ፡፡

የሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብር የቤተሰባቸውን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ ባለፈ ምርቶቻቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ በማቅረብ ኑሯቸውን ማሻሻሉን ተጠቃሚዎቹ ተናግረዋል፡፡

መጪውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግም ምርቶቻቸውን ለኅብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ዝግጅት ማድረጋቸውን ነው ለኢዜአ የገለጹት፡፡

እያጋጠማቸው ያለው የማምረቻ ቦታ እና ውሃ እጥረት ከተቀረፈ የሌማት ትሩፋት እያስገኘላቸው ካለው ተጠቃሚነት አኳያ ሥራቸውን የበለጠ ለማስፋት ፍላጎት እንዳላቸውም አመላካተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ባዩ ሽጉጤ በበኩላቸው÷ ከመሥሪያ ቦታ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮችን ከግንባታ ቁጥጥር ባለሥልጣን ጋር በመሆን ለመፍታት እየተሠራ ነው ብለዋል።

ከውሃ እጥረት ጋር በተያያዘም የጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮና በቤት ውስጥ ለተለያየ ነገር ጥቅም ላይ የሚውልን ውሃ መልሶ በማጣራት እንዲጠቀሙ የማስተማርና የማገዝ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!