አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራዔል የሃማስ ጠንካራ ይዞታ ነው ባለችው በደቡባዊ ጋዛ በሚገኘው ካን ዮኒስ ከተማ በታንክ እና በዓየር የታገዘ ጥቃት እያደረሰች መሆኗ ተሰምቷል፡፡
በከተማዋ የእስራዔል ወታደሮች እና የሃማስ ታጣቂዎች ከባድ የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡
የእስራዔል ወታደራዊ ኃይል ባለፉት 24 ሠዓታት በወሰደው የማጥቃት እርምጃ በአሥራዎች የሚቆጠሩ የሃማስ ታጣቂዎች መገደላቸውን አስታውቋል፡፡
የእስራኤል ምድር ጦር ጋዛ መግባቱን ተከትሎም በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቀያቸውን ጥለው መሰደዳቸው ተገልጿል፡፡
የነዋሪዎቹን ስደት ተከትሎም ተዛማች ወረርሽኝ በሽታ መከሠቱን ዘገባው አመላክቷል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በበኩሉ በሁኔታው ማዘኑን ገልጾ÷ ወደ ጋዛ እየደረሠ ያለው የዕርዳታ መጠንም ከጠበቀው በታች መሆኑን አስታውቋል፡፡
በሌላ በኩል እስራኤል ዕርዳታው ወደ ሥፍራው እንዳይደርስ ምንም አይነት እንቅፋት አለመፍጠሯን አስታውቃለች፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!