Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሃላባ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃላባ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ‘ሴራ’ በዓል በሆሳዕና ከተማ እየተከበረ ነው።

በአከባበር ሥነ-ሥርዓቱ በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሃላፊ መሐመድ ኑሪዬን (ዶ/ር ) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በመርሐ-ግብሩ የብሔረሰቡን ባህላዊ ምግብ፣ አልባሳት እና የሙዚቃ ትርዒት የማስተዋወቅ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

“ሴራችን የባህል ልውውጥና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መሰረታችን ነው፤ ሴራችን የአንድነታችን ማሳያ ድንቅምልክታችን ነው፤ ሴራችን በዘመናት የተፈጠሩ ባህላዊ እሴቶቻችንን መጠበቂያችን ነው” የሚሉ መልዕክቶችም እየተ ላለፉ ይገኛል።

Exit mobile version