አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ዶንግ ጁንን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር አድርጋ ሾመች።
ዶንግ ጁን የቀድሞ መከላከያ ሚኒስትር በይፋ ከሥራ ከተሰናበቱ ከሁለት ወራት በኋላ ነው የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት፡፡
የዶንግ ጁን ሹመት የቻይና ከፍተኛ የሕግ አውጪዎች ምክር ቤት ዛሬ በቤጂንግ ባካሄደው የብሄራዊ ሕዝባዊ ኮንግረስ ቋሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ይፋ መደረጉ ተጠቁሟል፡፡
እርምጃው የተወሰደው በተያዘው ዓመት መጀመሪያ ላይ ከፍተኛ የመከላከያ ባለስልጣናት ከሃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡
የ62 ዓመቱ ዶንግ በፈረንጆቹ ነሐሴ ወር 2021 የባህር ሃይል አዛዥ ሆነው ተሾመው እንደነበር አይዘነጋም።
ቀደም ሲልም የቻይና ወታደራዊ ደቡባዊ የጦር ልምምድ ዕዝ ምክትል አዛዥ በመሆን ማገልገላቸው ተጠቅሷል።
በዛሬው ዕለትም ተጨማሪ ዘጠኝ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት ከሃላፊነት እንደተነሱ በቋሚ ኮሚቴው ይፋ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።