አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ለ320 ሺህ ሰዎች የሕክምና አገልግሎት የመስጠት አቅም ያላቸው ጤና ጣቢያዎች ግንባታ በተለያየ ምዕራፍ እየተከናወነ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ ገለጸ።
የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ÷ እየተከናወነ ያለው የጤና ጣቢያዎች ግንባታ በከተማ ደረጃ አንዱ እስከ 40 ሺህ ሰዎችን ያስተናግዳል ተብሎ እንደሚታሰብ አብራርተዋል።
በከተማዋ 101 ጤና ጣቢያዎች እንደሚገኙም ገልጸው፤ በዚህ ዓመት በአቃቂ፣ ኮልፌና ቦሌ ክፍለ ከተሞች በሚገኙ አራት ወረዳዎች አዳዲስ ጤና ጣቢያዎች ለመገንባት ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።
የጤና ሚኒስቴርና የዓለም ጤና ድርጅት ባስቀመጡት መስፈርት መሠረት በከተማዋ ያለው የጤና ተቋማት ተደራሽነት በጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡
ጤና ጣቢያ በሌላቸው ወረዳዎች አዳዲስ ተቋማትን ከመገንባት ባሻገርም በነባር የጤና ተቋማት የማስፋፊያ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ዶክተር ዮሐንስ ጠቁመዋል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ከፍለው መታከም የማይችሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ የማኅበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት ከተማ አስተዳደሩ ለጤና ዘርፍ ሥምንት ቢሊየን ብር በጀት መድቦ እየሠራ መሆኑንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!