Fana: At a Speed of Life!

ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ስኬታማነት እየተሰሩ ባሉ ፕሮጀክቶች ምክክር ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን ስኬታማ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶች ላይ የምክክር መድረክ ተካሄዷል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስኬታማ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶች በቀጣይ የሚሰሯቸውን ስራዎች እንዲያቀርቡ በማድረግ ውጤታማ ሊያደርጓቸው በሚችሉ አፈፃፀም ላይ መሰረት በማድረግ እንዲሰሩ በጋራ መክረዋል፡፡

በፕሮጀክቱ ከተካተቱት ውስጥ የተከለሰውን የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ፣ ስታርታፕ፣ ዲጅታል ቢዝነስ፣ ኢኖቬቲቭ፣ የካምፓስ ኔትዎርክ፣ በኢ-ስኬታማ ስትራቴጂ አፈጻጸምንመት፣ በአይሲቲ ኢንፍስትራክቸር፣ የዲጂታል ኢኮኖሚ፣ የዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ወርክ ሾፖች፣ የብሄራዊ መታወቂያና ሌሎች ስራዎች ላይ ተወያይተውባቸዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) እንዳሉት ፥ ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢኮኖሚው ውጤት እንድታመጣ የአሰራር ስርዓቶችን በመገምገም ክፍተቶችን በቅንጅትና በፍጥነት በማረም እድገት ማስመዝገብ ይገባናል፡፡

ኢትዮጵያ እራሷን ስላላስተዋወቀች በገፅታ ግንባታ ላይ የሚሰራ የቴክኒክ ኮሚቴ ተቋቁሞ በስትራቴጂው የተፈፀሙ ውጤቶችን በሀገራዊ ሲምፖዚየም በማቅረብ ለህዝብ ከማስተዋወቅ አልፎ ለውጪ ሀገራት ግንዛቤ እንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑንም ነው የጠቆሙት፡፡

የዲጂታል ፋውንዴሽን እየተመራ ያለው ትልቅ በሆነው በመንግስት ሃብት ስለሆነ በተገቢው መንገድ በመተግበርና ከብክነት እንዲጠበቅ የክትትልና የግምገማ ስርዓታችን ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

በምክክር መድረኩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ሚኒስቴር፣ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን እና ብሔራዊ መታወቂያ መሳተፋቸውን ከኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.