Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ በሕገ- ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ በየቀኑ ከ630 ሺህ ዶላር በላይ ታጣለች ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በሕገ- ወጥ መንገድ ከሀገር በሚወጣ የቁም እንስሳት ንግድ በየቀኑ ከ630 ሺህ ዶላር በላይ እንደምታጣ ተገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አዘጋጅነት ሕገ-ወጥ ንግድን መከላከል ላይ ያተኮረ ሀገር አቀፍ ጉባዔ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በቀን ከ1 ሺህ 200 በላይ የቁም እንስሳት በሕገ-ወጥ መንገድ ከሀገር እንደሚወጡም የኢዜአ መረጃ ጠቁሟል፡፡

የሕገ-ወጥ ንግድ ሥልትና ዓይነት እየተቀያየረ መምጣቱ፣ የክትትልና የቁጥጥር ሥራው አጥጋቢ አለመሆኑ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈና ሕጉን የጠበቀ የግብይት ሥርዓትን ማስተግበር ላይ ክፍተቶች መኖራቸው ለሕገ-ወጥነቱ መስፋፋት በምክንያትነት እንደሚጠቀሱ በዘርፉ ላይ ጥናት ያደረጉት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር አለባቸው ንጉሴ (ዶክተር) ተናግረዋል፡፡

ከተቀባይ ሀገራት ጋር ሕጋዊ ሥምምነት ማድረግና ኅብረተሰቡ ሕገ-ወጦችን በመጠቆም ረገድ የበኩሉን እንዲወጣ ግንዛቤ መፍጠር እንዲሁም ከፀጥታ አካላት ጋር ማስተሳሰር እንደመፍትሔ የቀረቡ ሐሳቦች ናቸው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version