አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሠራ ያለው የሌማት ትሩፋት ተሥፋ ሠጭ ውጤቶች እየታዩበት መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የግብርና ሚኒስትር ደዔታ አማካሪ ዮሐንስ ግርማ (ዶ/ር)÷ከፋናብሮድካቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ “የሌማት ትሩፋት” በርካታ ውጤቶች እንደተገኙበት አብራርተዋል፡፡
ለአብነትም በ2015 በጀት ዓመት ከ41 ሚሊየን በላይ የዶሮ ጫጩት ማቅረብ መቻሉን አንስተዋል፡፡
በተያዘው በጀት ዓመት ከሐምሌ ወር ጀምሮ ላለፉት አምሥት ወራት ከ30 ሚሊየን በላይ የዶሮ ጫጩቶች ተፈልፍለው ለተጠቃሚው ማቅረብ እንደተቻለም ነው የገለጹት።
በዚህ ዓመት ከተያዙት ዕቅዶች መካከል 9 ነጥብ 8 ቢሊየን ሊትር ወተት ምርት እንደሚገኝበት ጠቁመዋል፡፡
በተጨማሪም ከ200 ሺህ ቶን በላይ የማር ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷልም ነው ያሉት፡፡
ከ130 ሺህ ቶን በላይ ዐሣ ለማምረትም ሚኒስቴሩ አቅዶ እየሠራ መሆኑን በመግለጽ በሌማት ትሩፋት ሀገራዊ ኢኮኖሚው ላይ የሚጠበቀውን ውጤት ለማስመዝገብ አሥፈላጊ ግብዓቶችን ማሟላት እና ድጋፍ ማድረግ ላይ እየተሠራ ነው ተብሏል፡፡
በዙፋን ካሳሁን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!