Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሩሲያ በጋዛ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በእስራዔል እና በጋዛ መካከል የቀጠለው የጦርነት አዙሪት በአስቸኳይ እንዲቋጭ አሳሰበች፡፡

የሀገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ታስ ለተሰኘው የሀገራቸው ዜና አገልግሎት በሠጡት ቃለ መጠይቅ፥ በጋዛ እና በመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት የሁለቱን ወገኖች መቋጫ የለሽ ጦርነት ማቆም አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገለጻ በሁለቱ ወገኖች መካከል ሠላም ከጠፋ 75 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

“ሁኔታው መቋጫ የሚያገኝ አይመስልም ሲሉ” ነው ሐሳባቸውን አፅንዖት የሠጡት፡፡

ይልቁንም በሁለቱ ወታደራዊ ኃይሎች መካከል በሚፈጸሙ ጥቃቶችና የበቀል ምላሾች መካከል የጋዛ ሕዝብ ተደጋጋሚ መከራ እየተቀበለና የግጭታቸው ውጤት ገፈት ቀማሽ እየሆነ ብለዋል፡፡

ላቭሮቭ “ለሽብር ጥቃት የተሠጠ ምላሽ እያሉ ሕዝቡ ላይ በጅምላ ለሚፈጸመው ቅጣት ሕጋዊ ከለላ መስጠት ዓለም አቀፉን ሰብዓዊ ሕግ መጣስ ነው” ማለታቸውንም አር ቲ ዘግቧል፡፡

“የሩሲያ አቋም በፀጥታው ምክር ቤት እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ እንዲሁም በአረብ የሠላም ማዕቀፍ ውሳኔ ላይ የተመሠረተ ነው” ሲሉም አክለዋል፡፡

የዓለምአቀፍ አደራዳሪዎች ሚና ሁለቱ ወገኖች እንዲነጋገሩ እና ችግሮቻቸውን ሁሉ እራሳቸው እንዲፈቱ መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

ይህ እስካልሆነ ድረስ ግን ደም መፋሰሱ ይቀጥላል ሲሉም ነው ሥጋታቸውን የገለጹት፡፡

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version