ስፓርት

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ከዌስትሃም እንዲሁም ቶተንሃም ከብራይተን የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

By Mikias Ayele

December 28, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ በበዓል ሰሞን መርሐ ግብር አርሰናል ከዌስትሃም እንዲሁም ቶተንሃም ከብራይተን ዛሬ ምሽት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

አርሰናል ከዌስትሃም ዩናይትድ የሚያደርጉት ጨዋታ ምሽት 5፡15 የሚደረግ ሲሆን በጨዋታው መድፈኞቹ የፕሪሚየርሊጉን መሪነት ከሊቨርፑል መልሰው ለመረከብ ወደ ሜዳ ይገባሉ፡፡

በጨዋታው መድፈኞቹ ከፍተኛ የአሸናፊነት ግምት ሲሰጣቸው የአሰልጣኝ ዴቪድ ሞዬሰ ቡድን ዌስትሃም ቀላል ተጋጣሚ እንደማይሆን ይጠበቃል፡፡

በምሽቱ ጨዋታ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ መጠነኛ የአሰላለፍ ለውጥ ያደርጋሉ የተባለ ሲሆን ስሚዝ ሮው፣ ጆርጊኒሆን እና ትሮሳርድን በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ሊያካትቱ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡

በሌላ ጨዋታ ምሽት 4፡30 ብራይተን ከቶተንሃም ጨዋታቸውን ሲያደርጉ ተመጣጣኝ የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቷቸዋል፡፡

በጉዳት እየታመሰ የሚገኘው የአሰልጣኝ አንጄ ፖስትኮግሉ ቡድን ቶተንሃም ጀምስ ማዲሰን እና ሮሚሮ በረጀም ጉዳት ምክንያት በዛሬው ጨዋታ አይሰለፉም፡፡

በብራይተን በኩል ሶሊ ማርች ፣ ጁሊዮ ኢንሲሶ እና ፔርቪስ ኢስቱፒናን ከጉዳት መልስ ሊሰለፉ ይችላል የተባለ ሲሆን ላምፕቴይ፣ አዳም ዌብስተር እና ሚቶማ ከዛሬው ጨዋታ ውጭ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ቀደም ሲል በተደረጉ የቦክሲንግ ደይ እና የበዓል ሰሞን ጨዋታዎች ታላላቆቹ ማንቼስተር ዩናይትድ፣ ሊቨርፑል፣ ቼልሲ እና ማንቼስተር ሲቲ ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው፡፡