አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን ሰላምና መግባባት እስኪሰፍን ድረስ በቁርጠኝነት እንሰራለን ሲሉ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ሃሳብ፤ የሱዳንን የነፃነት ቀን እና አዲሱን የፈረንጆችን ዓመት ስናከብር ሃሳቤ ከሱዳን ህዝብ ጋር ነው ብለዋል፡፡
በሱዳን ለሚገኙ ወንድሞች እና እህቶች ሰላም ለማምጣት እንዲሁም ወደመደበኛ ሁኔታ ለመመለስ በምንጥርበት በዚህ ጊዜ ተስፋችን ብሩህ ነው ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡
የሱዳን ህዝብ የነጻነት ትግል ፋና ሆኖ የቆመ ነው ሲሉም ዋና ፀሃፊው ገልጸዋል፡፡
የሱዳን ህዝብ እየገጠመው ያለውን ፈተና በትዕግስት አልፎ በፅናቱ የሚያንጸባርቅ ውጤት እንደሚያመጣ ገልጸው፥ ይህን ጊዜም አብረን እናልፈዋለን ሲሉም አንስተዋል፡፡
በዚህም በሱዳን ሰላምና መግባባት እስኪሆን ድረስ በቁርጠኝነት እንሰራለን ሲሉ ዋና ጸሐፊው አረጋግጠዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!