የሀገር ውስጥ ዜና

በያቤሎ ጠቅላላ ሆስፒታል መንታ ህጻናት ተጣብቀው ተወለዱ

By Amele Demsew

December 27, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቦረና ዞን ያቤሎ ወረዳ በያቤሎ ጠቅላላ ሆስፒታል መንታ ህጻናት ተጣብቀው መወለዳቸው ተገለጸ።

የያቤሎ ጠቅላላ ሆስፒታል የጽንስና ማህጸን ስፔሻሊስት ዶክተር ዋሪዮ ዱባ እንደተናገሩት፤ የተወለዱት ህጻናት የተጣበቁት በደረት አካባቢ ነው።

በሆስፒታሉ የቀዶ ህክምና ክፍል ሐኪም የሆኑት ዶክተር ግዛቸው ታከለ በበኩላቸው ተጣብቀው ለተወለዱት ህጻናት ተጨማሪ ምርመራና ህክምና እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

በአዲስ ታምራት