Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

እስራዔል ለአሜሪካ የኤሌክትሮኒክስና ቺፕሶች ማምረቻ ግንባታ 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ልትሰጥ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የአሜሪካው “ኢንቴል ኮርፖሬሽን” በ25 ቢሊየን ዶላር መዋዕለ-ንዋይ በደቡባዊ የእስራዔል ለሚገነባው የኤሌክትሮኒክስ ቁሶች እና ቺፕሶች ማምረቻ የሚውል የ3 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ሥጦታ ከእስራዔል እንደቀረበለት ተገለጸ፡፡

እስራዔል ከአሜሪካው የኤሌክትሮኒክስ ቁሶች እና ቺፕሶች አምራች “ኢንቴል ” ጋር ልታስር የተሰናዳችው ውል በታሪኳ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትልቁ ነው ሲሉ የሀገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ገልጸዋል፡፡

ዛሬ የተሠማው አዲሱ የልማት ዜና ሀገሪቷ በጋዛ ሠርጥ ከባድ ጦርነት እያካሄደች ባለበት ወቅት መሆኑን ዘገበው አልጀዚራ ነው፡፡

እስራዔል ከኩባንያው ጋር ያደረገችው ሥምምነት ግዙፉ የአሜሪካ ኩባንያ ሀገሪቷ ለምታደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ያለውን ድጋፍ ያሳየ ነውም ተብሎለታል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ለሚቀጥለው አሥር ዓመት የሚገዛውን ቁስ እና አገልግሎት ከእስራዔል አቅራቢዎች እንደሚገዛም በስምምነቱ ተመላክቷል፡፡

ኢንቴል በበርካታ ሺህዎች የሚቆጠር የሥራ ዕድል ለእስራዔላውያን ይፈጥራልም ተብሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version