Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጤናማ ህይወትን ለመምራት

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጤናማ መሆን ማለት በአዕምሮ፣ በአካልና በስሜት ሙሉ ጤንነት ሲሰማን ማለት ነው፡፡

ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን መከተል በበሽታ እንዳንጠቃ ከማገዙም በላይ ጤናችን ስንጠብቅ ለራሳችን ያለን ግምት መልካም እንደሚሆን የተለያዩ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡

ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ደስተኛ፣ የተረጋጋና ስኬታማ ህይወት እንድንኖር ይረዳናል፡፡

ምንም እንኳን የተለያዩ ውጫዊና ውስጣዊ ሁኔታዎች ጤናማ ህይወትን ለመምራት አሉታዊ ተጽዕኖ ቢፈጥሩም አኗኗራችንን እና ልማዶቻችንን በመቀየር ጤናማ ህይወት መኖር እንደሚቻል ነው ጥናቶች የሚያመላክቱት።

ጤናማ ህይወት ለመኖር የሰው ልጅ የተለያዩ የህይወት ዘይቤዎችን ይተገብራል፡፡

ከእነዚህም መካከል ዋና ዋናዎቹ፦

• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣
• የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣
• ክብደትን መለካትና መቆጣጠር፣
• በቂ ውሃ መጠጣት፣
• ለረዥም ጊዜ ያለመቀመጥና ኮምፒውተርና ሌሎች ስክሪን ላይ የምናጠፋውን ጊዜ መቀነስ፣
• በቂ እንቅልፍ መተኛት፣
• ከመጠን ያለፈ አልኮል ያለመውሰድ፣
• ቁጣና መሰል ስሜቶችን መቆጣጠር፣
• ጭንቀትን ማስወገድ፣
•የጤና ክትትል ማድረግና መሰል የጤናማ አኗኗር ዘይቤዎች ይጠቀሳሉ፡፡

በተጨማሪም ከሰዎች ጋር ያለንን ማህበራዊ ግንኙነት በትኩረት መመልከት እንደሚያስፈልግ የጤና ባለሙያዎች ይመክራሉ።

ከጓደኞች፣ ከቤተሰብና ጎረቤት እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ጋር ያለንን የዕለት ተዕለት ግንኙነት ማሻሻልና መልካም ማድረግ ለጤናማ ህይወት አስፈላጊ እንደሆነ የሜዲሲን ኔት መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version