Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ወጣቶች ሥራ ፈጣሪና ለልማት የሚተጉ እንዲሆኑ በትኩረት ይሰራል – አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ሥራ ፈጣሪ እና ለልማት የሚተጉ እንዲሆኑ ለማስቻል በትኩረት እንደሚሰራ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መሥተዳደሩና ሌሎች የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች በጎፋ ዞን የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።

የሥራ ኃላፊዎቹ ከልማት ሥራዎቹ የአፈጻጸም ጉብኝት በተጨማሪ በዞኑ በሥምንት ወር ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀውን የጋልማ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ህንጻን መርቀዋል፡፡

ኮሌጁ ለዞኑ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ብቁ ወጣቶችን ማፍራት የሚያስችል መሆኑን አቶ ጥላሁን ገልጸዋል።

ርዕሠ-መሥተዳድሩ ከልማት ሥራዎች ጉብኝት ጎን ለጎን ከጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይታቸውም፤ በክልሉ ያለውን የመልማት ዓቅም ወደ ተግባር ለመቀየር የተጀመሩና የሚጀመሩ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ የክልሉን ልማት እውን ይደረጋል ብለዋል።

ለዚህም ከህዝቡ ጋር በመቀራረብ በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

በፍሬሕይወት ሰፊው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version