Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአማራ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል 11ሺህ ኩንታል የበቆሎ ዱቄት ወደ ሥፍራው እየተጓጓዘ መኾኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 15 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በድርቅ ለተጎዱ የኀብረተሰብ ክፍሎች የሚውል 11ሺህ ኩንታል የበቆሎ ዱቄት ድጋፍ መደረጉን አመልድ – ኢትዮጵያ ገለጸ።

ድጋፉ በሰሜን ጎንደር በየዳ፣ ጃናሞራ እና ጠለምት እንዲሁም በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በሰቆጣ፣ ፃግብጂ እና አበርገሌ ወረዳዎች በድርቅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚከፋፈል የአመልድ ኢትዮጵያ ምክትል ዳይሬክተር ሺብሬ ጆርጋ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ምክትል ዳይሬክተሯ እንዳሉት ፀደይ ባንክ፣ ዓባይ ባንክ እና በላይነህ ክንዴ ፋውንዴሽን በጠቅላላው 70 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

አመልድ ኢትዮጵያ ድጋፉን እያስተባበረ በተገኘው ገንዘብ ጥራቱን የጠበቀ 11ሺህ ኩንታል የበቆሎ ዱቄት ተገዝቶ 80 ሺህ ለሚኾኑ በድርቁ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ለማድረስ በማጓጓዝ ላይ ነው ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

የፀደይ ባንክ ፕሬዚዳንት መኮንን የለውምወሰን “በክልሉ በተፈጥሮ እና በሰው ሠራሽ ምክንያት ለችግር የተዳረጉ ወገኖችን ሕይወት ለመታደግ አመልድ ኢትዮጵያ የዕለት ደራሽ ምግብ ገዝቶ እንዲያቀርብ 50 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገናል” ብለዋል፡፡

አቶ መኮንን ሌሎች ባንኮች እና ኢንሹራንሶችም የእነሱን አርዓያ እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Exit mobile version