አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእስራዔልና በሃማስ መካከል የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ በቀይ ባህር የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ብቸኛው መንገድ በጋዛ የተኩስ አቁም ማድረግ መሆኑን ባለሙያዎች ገለፁ፡፡
በየመን የሚገኙት የሃውቲ አማፂያን ቀይ ባህር “የእሳት አውድማ” ከመሆኑ በፊት አሜሪካ እና አጋሮቿ አካባቢውን በፍጥነት ለቀው ይውጡ ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ማስጠንቀቂያው የተላለፈው ንብረትነቷ የጋቦን የሆነችውና የህንድ ሰንደቅ ዓላማ ስታውለበልብ በነበረች ድፍድፍ ነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ በሰው አልባ አውሮፕላን አማካኝነት ጥቃት በመድረሱና አሜሪካ ለጥቃቱ የሃውቲ አማጽያንን ተጠያቂ በማድረጓ ነው፡፡
ይሁንና የሃውቲ ቃል አቀባይ መሐመድ አብዱሰላም ጥቃቱን ሃውቲ እንዳልፈፀመ በመግለፅ ክሱን ያጣጣለ ሲሆን÷ ከዚህ ምስጢራዊ የሚሳኤል ጥቃት ጀርባ ያለው የአሜሪካ ባህር አውዳሚ ኃይል ነው ሲል አስተባብሏል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያሻቀበ የመጣው የቀይ ባህር ውጥረት ዋና ዋና የመርከብ እና የነዳጅ ኩባንያዎች በወሳኙ የባህር ንግድ መስመር ላይ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲያቆሙ ምክንያት መሆኑ ይገለፃል፡፡
ይህም በዓለም አቀፍ ምጣኔ ሀብት ላይ ቀውስ ያስከትላል የሚል ስጋት መፍጠሩን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።
በጋዛ ያለው ግጭት ለአሁኑ የቀይ ባህር ቀውስ መንስኤ እንደሆነ የሚያነሱት ባለሙያዎችም የቀይ ባህርን ውጥረት ለማርገብ ብቸኛው መንገድ በጋዛ የተኩስ አቁም ማድረግ መሆኑን አመላክተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!