Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባህርዳር እና ዱጃንየ ከተሞች የእህትማማችነት ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራ ልዑካን ቡድን በቻይና የሥራ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡

ልዑኩ ከጉብኝቱ ጎን ለጎንም የባህርዳር እና የቻይናዋ ዱጃንየ ከተሞችን የእህትማማችነት ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱን የባህርዳር ከተማ ከንቲባ ጎሹ እንዳለማው እና የዱጃን ከተማ ከንቲባ ጃንያ ዳን ተፈራርመዋል፡፡

በስምምነቱ ሁለቱ ከተሞች በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በቱሪዝም፣ በፓርክ ልማትና አስተዳደር እንዲሁም በአረንጓዴ ልማት ሥራዎች ዙሪያ በቀጣይ በጋራ ለመስራት ቃል ገብተዋል፡:

በተጨማሪም በከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራው የልዑካን ቡድን የቻይና ፓርክ ከተማ ተብላ በምትታወቀው ቼንዱ ከተማ የተለያዩ ፓርኮችን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል::

በጉብኝቱ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው እና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎችና ከንቲባዎች እንዲሁም ባለሙያዎች መሳተፋቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ከኢትዮጵያ ከተሞች ጋር በትብብር ለመስራት የቻይና ከተሞች ላሳዩት ተነሳሽነትና በቻይና ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበልም ከንቲባ አዳነች ምስጋ አቅርበዋል::

Exit mobile version