አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ2 ሺህ 800 በላይ አዳዲስ የመንገድ ዳር መብራቶችን ለመዘርጋት ሥራ መጀመሩን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ምክትል ኃላፊ ኢንጂነር ታከለ ሉላና፥ ለሥራው ከ950 ሚሊየን ብር በላይ በጀት እንደተያዘ ተናግረዋል።
አሁን ላይ ምሰሦዎችን የመትከል ሥራ መጀመሩንም ነው የጠቆሙት፡፡
የመንገድ ዳር መብራቶቹን በሥድስት ሎቶች እና በ45 መንገዶች የመዘርጋት ሥራ ይከናወናልም ብለዋል።
ባለሥልጣኑ በጃፓን መንግሥት ድጋፍ የተለያዩ ማሽኖች እና ተሽከርካሪዎች መግዛቱን ጠቅሰው፥ ተቋሙ ያከናወነው የዐቅም ግንባታ ለሥራው ስኬታማነት አስተዋፅዖ አድርጓልም ነው ያሉት።
ኅብረተሰቡም የመንገድ ዳር መብራቶች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ግለሰቦችን ለፀጥታ አካላት እንዲያሳውቅ ጠይቀዋል፡፡
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ለብልሽት የተዳረጉ የመንገድ ዳር መብራቶችን በመጠገን ሰፊ ሥራ እየሰራ መሆኑም ጠቁመዋል፡፡
በማርታ ጌታቸው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!