አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 10 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቡና ወጪ ንግድ ለመሰማራት ፍላጎት ላሳዩ የቻይና ባለሐብቶች ገለፃ ተደረገላቸው፡፡
በግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ-ግብሩ የቻይና የመንግሥት እና የንግዱ ማኅበረሰብ ቡድን አባላት ተሳትፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቡና ላኪ ድርጅቶች እና የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን፥ በኢትዮጵያ የቡና ወጪ ንግድ አሰራር ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለ ሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ÷ ኢትዮጵያ በዓመት ወደ 8 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ቡና ወደ 10 የዓለም ሀገራት እንደምትልክ ገልጸዋል፡፡
የቻይና ልዑካን ቡድንም ከኢትዮጵያ ቡና ላኪ ባለሐብቶች ቀጣይ የአሠራር ተሞክሮ በመውሰድ የኢትዮጵያን ቡና ተረክበው ወደ ቻይና ለመላክ እና በዘርፉ ለመሰማራት ያላቸውን ፍላጎት አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ከውጭ ምንዛሬ ጋር ተያይዞ በቻይና ያጋጠማቸውን ችግር እና ቅሬታ ለልዑካን ቡድኑ አቅርበዋል፡፡
የቻይና – ኢትዮጵያ ወዳጅነትና ትብብር ማኅበረሰብ ሴክሬተሪ ጀነራል ሺ ፊንጅ ችግሩ እንደሚቃለል መናገራቸውን ከባለሥልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!