አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በኩዌት ኤሚር ናዋፍ አል-አሕመድ አል-ሳባህ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ፡፡
ፕሬዚዳንቷ የኩዌት ኤሚር ሼኽ ናዋፍ አል አሕማድ አል ሳባህ ከዚህ ዓለም በሞት መለየትን አስመልክቶ ለተኳቸው ለኤሚር ሼኽ መሻል አል አሕማድ አል ሳባህ፣ ለንጉሣዊ ቤተሰብና ለሀገሪቱ ሕዝብ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ስም ነው ሃዘናቸውን የገለጹት፡፡
የኢትዮጵያና ኩዌት ግንኙነት ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጀምሮ የቆየ ሲሆን÷ በኩዌት ፈንድ አማካኝነት ለኢትዮጵያ ማህበራዊና ኢካኖሚያዊ ዕድገት የሚያደርጉት አስተዋጽኦም ከፍተኛ ነው መባሉን የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
በኢራቅና ኩዌት ጦርነት ወቅት ኢትዮጵያ የኩዌትን ወረራ በይፋ መቃወሟም ይታወሳል።