አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 10 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጋራ መስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ኢ/ር) ስለኢንስቲትዩቱ ሥራዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡
ሁለቱ ተቋማት በቴክኖሎጂ፣በአቅም ግንባታ፣ በምርምር እና ልማት ስራዎች አብረው መስራት እንደሚችሉ በመድረኩ ተነስቷል፡፡
የቻይና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራር ሬን ሆንግቦ በበኩላቸው፥ ተቋማቸው ለኢንስቲትዩቱ የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ ዝግጁ እንደሆነ መግለጻቸውን የኢንስቲትዩቱ መረጃ ያመላክታል፡፡