Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዶናልድ ትራምፕ ከኮሎራዶ ግዛት የምርጫ ውድድር ተሰረዙ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 10 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቀጣዩ አመት በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በኮሎራዶ ግዛት አይወዳደሩም ተባለ።

የኮሎራዶ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትራምፕ በግዛቲቱ የምርጫ ውድድር መሳተፍ አይችሉም ሲል ብይን ሰጥቷል።

ለዚህ ደግሞ ትራምፕ ከሶስት አመት በፊት በካፒቶል ሂል ‘በመንግስት አሥተዳደር ላይ አመፅ’ መቀስቀሳቸውን ጠቅሷል።

ይህን ተከትሎም በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ትራምፕ በግዛቲቱ መወዳደር እንደማይችሉ መግለጹን ቢቢሲ ዘግቧል።

የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በተመለከተ የዶናልድ ትራምፕ የምርጫ አስፈጻሚዎች ለአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ እንደሚሉ ገልጸዋል።

የትራምፕ አማካሪ ውሳኔውን ‘አግባብነት የሌለው’ በማለት ተችተውታል።

ትራምፕ በኮሎራዶ ግዛት ከምርጫው ቢሰረዙም አሁንም ግን በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው በሌሎች ግዛቶች ዕጩ ሆነው መወዳደር ይችላሉ ተብሏል።

በኒው ሃምፕሻየር፣ ሚኒሶታ እና ሚቺጋን ትራምፕን ከምርጫው ለመሰረዝ የተደረገው ሙከራ ይሁንታን ሳያገኝ መቅረቱንም ዘገባው አመላክቷል።

Exit mobile version