Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሠራዊቱ ግዳጅ ውስጥ ሆኖ በሁሉ አቀፍ የግብርና ልማት ላይ ያስገኘው ውጤት የሚደነቅ ነው-ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሠራዊቱ ሀገርን በማዳን ውስብስብ ግዳጅ ውስጥ ሆኖ በሁሉ አቀፍ የግብርና ልማት ላይ እያሳየ ያለው እምርታና ያስገኘው ውጤት የሚደነቅ ነው ሲሉ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ገለጹ።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የመከላላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ባዘጋጀው አውደ ጥናት ላይ ተገኝተው እንደገለጹት÷ ሰራዊቱ በሚኖርበት ቀጠና የግብርና ስራዎች ላይ በመሳተፍ እያደረገ ያለው የልማት እንቅስቃሴ የሚደነቅ ነው፡፡

አመራሩና አባላቱ ከአካባቢው የግብርና ባለሙያዎች እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እያከናወኑ ላሉት ውጤታማ የልማት ተግባር ፊልድ ማርሻል ብርሁኑ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

“በቀጣይም የተቋማችን ሁሉም ክፍሎች የተሰጣቸውን ሀገራዊና ተቋማዊ ግዳጆች ከመፈፀም ጎን ለጎን በእርሻው መስክ ሊሰማሩ ይገባል” ሲሉም ማሳሰባቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version