አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ የግብፅን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለ3ኛ ጊዜ ማሸነፋቸውን የሀገሪቱ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡
በዚህም አል ሲሲ ግብፅን ለቀጣይ 6 ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ያገለግላሉ ነው የተባለው፡፡
የግብፅ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዳስታወቀው÷ በ2024 የግብፅ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ፕሬዚዳንት አብዱልፋታህ አል ሲሲ 89 ነጥብ 6 በመቶ ድምፅ በማግኘት ለ3ኛ ጊዜ አሸንፈዋል፡፡
በምርጫው ከተመዘገቡ 67 ነጥብ 3 ሚሊየን መራጮች 44 ነጥብ 7 ሚሊየን ዜጎች መሳተፋቸውም ተገልጿል፡፡
በምርጫው የህዝብ ሪፐብሊካን ፓርቲ 4 ነጥብ 5 በመቶ፣ የግብፅ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ 4 በመቶ እንዲሁም ዋፍድ ፓርቲ 1 ነጥብ 9 በመቶ ድምፅ ማግኘታቸው ተመላክቷል፡፡
በፈረንጆቹ ታህሳስ 11 እስከ 13 ቀን 2013 በተደረገው የድምፅ አሰጣጥ በ121 የተለያዩ ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ግብፃውያን ኤምባሲዎችን በመጠቀም በምርጫው ተሳትፎ ማድረጋቸውን አህራም ኦንላይን ዘግቧል፡፡