የሀገር ውስጥ ዜና

ክልሎቹ በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ እየተወያዩ ነው

By Amele Demsew

December 18, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ እና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊዎች በአዋሳኝ አካባቢዎች የሠላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በቡታጅራ ከተማ እየመከሩ ነው።

የውይይቱ አላማ ክልሎቹ በሰላምና ጸጥታ ጉዳይ ላይ በቅንጅት በመስራት በአዋሳኝ አካባቢዎች የሚኖሩ ህዝቦች ሰላም፣ ፀጥታና ደህነትን ማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

በውይይቱ ፅንፈኝነትንና አክራሪነትን በጋራ ለመከላከል ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ውይይቱ በሠላም ሚኒስቴር አስተባባሪነት የሚካሄድ ሲሆን፣ የመንግስታት ግንኙነት በኢትዮጵያ ፌዴራል ሥርዓት ሰነድ እና የሁለቱን ክልሎች ነባራዊ ሁኔታ የሚያሳይ የመነሻ ሰነድ ቀርቦ ውይይት የሚደረግበት ይሆናል።