Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በብድር የተሰጠ 83 ሚሊየን ብር ተዘዋዋሪ ገንዘብ ለማስመለስ እየሰራ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በብድር የተሰጠ 83 ሚሊየን ብር ተዘዋዋሪ ገንዘብ ለመመለስ እየሰራ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስራ እና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ኮማንደር ኢዶሳ ጎሹ ከፋና ብሮድካስቲንግ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፥ ባለፉት ዓመታት በክልሉ ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ከ83 ሚሊየን ብር በላይ ብድር ተሰጥቷል፡፡

በዚህ ዓመትም 4 ሺህ 142 ስራ ፈላጊዎች በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፍ ተደራጅተው ወደ ስራ መግባቸውንም ነው የገለጹት፡፡

ምክትል ኃላፊው ወጣቶቹ ውጤታማ እንዲሆኑ ክትትልና ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉም ተናግረዋል።

ሆኖም ግን አብዛኛው የብድር ገንዘብ አለመመለሱ የብድር አቅርቦት ላይ እክል ፈጥሯልም ነው ያሉት።

ከዚህ ጋር በተያያዘም ተጨማሪ የስራ እድል ለመፍጠር በተዘዋዋሪ ብድር የተሰራጨውን ገንዘብ ለመሰብሰብ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በአልማዝ መኮንን

#Ethiopia #benishangulgumuzregion

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version