የእስራዔል ጦር በስህተት ሶስት ታጋቾች መግደሉን አስታወቀ
አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 6 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራዔል ጦር በስህተት ሶስት ታጋቾች መግደሉን አስታወቀ።
ጦሩ በጋዛ ባካሄደው ዘመቻ ታጋቾች ‘እንደ ስጋት’ በስህተት ተለይተው በተፈጸመ ጥቃት መገደላቸውንም ነው የገለጸው።
በስህተት የተገደሉት ዮታም ሃዪም፣ ሳሚር ታላልክ እና ኤለን ሻምሪዝ የተባሉ ወጣቶች መሆናቸውንም የእስራዔልን ጦር ዋቢ ያደረገው የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል።
ትናንት ከተፈጸመው ስህተት ጋር ተያይዞም ጉዳዩ ላይ ምርመራ እያደረኩ ነው ያለው ጦሩ ለተጎጅ ቤተሰቦች የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ገልጿል።
ካለፈው የጥቅምት ሰባቱ የሃማስ ጥቃት በኋላ ከ100 በላይ ሰዎች በጋዛ ታግተው እንደሚገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ።
እስራዔላውያንም በሃማስ የታገቱ ዜጎች በሰላም ወደ ቤታቸው እንዲመለሱና መንግስት የእስረኞች ልውውጥ በማድረግ የዜጎችን ህይወት እንዲታደግ እየጠየቁ ነው።
በእስራኤል ሃማስ ጦርነት እስካሁን ከ18 ሺህ 800 በላይ ፍልስጤማውያን ለህልፈት መዳረጋቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴርን ዋቢ ያደረገው ዘገባ ያመላክታል።
በእስራዔል በኩል ደግሞ ከ1 ሺህ 200 በላይ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውንም ነው መረጃው የሚያመላክተው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!