Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ሰላም የምትፈጥረው ግቧ ሲሳካ ብቻ ነው -ፕሬዚዳንት ፑቲን

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ሰላም የምትፈጥረው ወደ ጦርነት ያስገቧት ጥያቄዎች ሲመለሱና ግቧ ሲሳካ ብቻ ነው ሲሉ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንት ፑቲን ይህንን ያሉት የሩሲያ -ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ የመጀመሪያው በሆነው ማራቶን የዜና ኮንፈረንስ ላይ በቀረቡበት ወቅት ነው፡፡

የፕሬዚዳንቱ መግለጫ በዩክሬን በሚካሄደው ልዩ ዘመቻ ላይ ያተኮረ ሲሆን÷ በሁሉም ግንባሮች ያለው ጦርነት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በቀጥታ ቴሌቪዥን ሥርጭት በተላለፈው መግለጫቸው÷ “የሩሲያን ሉዓላዊነት መጠበቅ ግዴታችን ነው”፤ “ሉዓላዊነቷ የተደፈረች ሀገር እንድትኖረን አንፈቅድም “ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የሩሲያ ኢኮኖሚ በጦርነቱ ወቅት እንኳን እድገት እያሳየ መሆኑንም ነው በመግለጫቸው አጽንኦት የሰጡት፡፡

“በዩክሬን ሰላም የሚኖረው እኛ ግባችን ስናሳካ ብቻ ነው፤ ጦረነቱን ስንጀምር እናሳካለን ያልናቸውን ግቦች መቼም ቢሆን አንቀይርም” ማለታቸውንም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.