ከ80 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ሥማርት ሥልኮችና የሞባይል ሥክሪኖች ተያዙ

By Alemayehu Geremew

December 13, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከ80 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ኮንትሮባንድ ሥማርት ሥልኮችና የሞባይል ሥክሪኖች መያዙን አስታወቀ፡፡

የኮንትሮባንድ ቁሶቹ የተያዙት በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት አርበረከቴ መቆጣጠሪያ ጣቢያ መሆኑን የጉምሩክ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ተደብቀው ሊተላለፉ የነበሩት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች 61 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው 2 ሺህ 730 ስማርት የስልክ ቀፎዎች ፣ ከ19 ሚሊየን ብር በላይ የሆኑ 12 ሺህ 700 የሞባይል ስክሪኖችና 63 ሺህ ብር የሚያወጡ የሞባይል ቻርጀሮች መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡