Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ የሚተገብረውን የሰብአዊ እገዛ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ የሚተገብረውን የሰብአዊ እገዛ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ማሪያና ስፓልያሪች ጋር ተወያይተዋል።

በስዊዘርላንድ ጄኔቫ በተካሄደው ውይይት ኢትዮጵያ ከተቋሙ ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችላት ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡

በተጨማሪም÷ አለምአቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ እያደረጋቸው ያሉ የሰብአዊ ድጋፍ ስራዎች ቁልፍ መሆናቸውን በማንሳት የሚሰጣቸው ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቶ ደመቀ ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ ሰላምን ለማፅናት እና በመልሶ ግንባታ እየተሰሩ ስለሚገኙ ስራዎችም አቶ ደመቀ መኮንን ለፕሬዚዳንቱ ገለፃ ማድረገቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የአለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ማሪያና ስፓልያሪች በበኩላቸው÷ ተቋማቸው በኢትዮጵያ የሚተገብረውን የሰብአዊ እገዛ አጠናክሮ ከእንደሚቀጥል ተናግረዋል።

Exit mobile version