Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በጎንደር ከተማ 872 ተጠርጣሪዎች የተሃድሶ ሥልጠና ወስደው ሕብረተሰቡን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩ 872 ተጠርጣሪዎች የተሃድሶ ሥልጠና እና የምክር አገልግሎት ተሰጥቷቸው ሕብረተሰቡን መቀላቀላቸውን ኮማንድ ፖስቱ ገለጸ፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ በጎንደር ከተማ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ጋር ውይይት አድርጓል።

መርማሪ ቦርዱ በከተማዋ በጊዜያዊ ማቆያ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች የሰብዓዊ መብት አያያዝ የጎበኘ ሲሆን በጉብኝቱም ተጠርጣሪዎቹ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ማረጋገጡን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የሰሜን ምዕራብ ኮማንድ ፖስት የጎንደር ቀጣና ሰብሳቢ ብርጋዴር ጄኔራል ዋኘው አለሜ እንደገለጹት÷ በቀጣናው 433 ተጠርጣሪዎች የተሃድሶ ሥልጠና ወስደው ወደ ሕብረተሰቡ ተቀላቅለዋል።

በተጨማሪም÷ 439 ተጠርጣሪዎች የግንዛቤና የምክር አገልግሎት ተሰጥቷቸው ማኅበረሰቡን የተቀላቀሉ መሆኑን ገልፀዋል።

በጎንደር ጊዜያዊ ማቆያ በቁጥጥር ሥር ውለው ከሚገኙ ተጠርጣሪዎች መካከልም 78ቱ በቅርቡ የተሃድሶ ሥልጠና ይገባሉ ብለዋል።

Exit mobile version