አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ አዲሱን ‘የዓየር መንገድ ከተማ’ ግንባታ በአራት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሠራ መሆኑን ገለጸ፡፡
ዓየር መንገዱ “ኤርፖርት ሲቲ” ብሎ የሚጠራውን ግንባታ ለመጀመር ከጫፍ የደረሰው እየጨመረ የመጣውን የደንበኞች ፍላጎት ለማርካት መሆኑን የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የንግድ ሥራ ዘርፍ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ለማ ያደቻ ተናግረዋል፡፡
የ ‘ዓየር መንገድ ከተማው’ ካልተገነባ ዓየር መንገዱ በዘርፉ እያስመዘገበ ካለው ፈጣን ዕድገት አንጻር እንደሚፈተን ከግምት ውስጥ በማስገባት ፕሮጀክቱ መታቀዱን አብራርተዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 5 ቢሊየን ዶላር በጀት የተያዘለት ሲሆን፥ በዓመት 100 ሚሊየን መንገደኞችን ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል።
አሁን ላይ ዓየር መንገዱ በኦሮሚያ ክልል ከቢሾፍቱ ከተማ ጥቂት ወጣ ብሎ በሚገኝ ሥፍራ የመጀመሪያውን የ ‘ዓየር መንገድ ከተማ’ ግንባታ ለማስጀመር በዝግጅት ላይ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ ዘመናዊ ሆቴሎች ፣ ከቀረጥ ነፃ የግብይት ሥፍራና የካርጎ ሎጂስቲክስ ማዕከል እንደሚኖረው ተጠቁሟል፡፡
የአዋጭነት ጥናቱን በማጠናቀቅም ለዓለም አቀፍ ጨረታ ለማውጣት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!