አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳይ በጦር መርከቧ ላይ በየመን ሰው አልባ አውሮፕላኖች የተሰነዘረባትን ጥቃት ማክሸፏን ገለፀች፡፡
የፈረንሳይ ጦር በቀይ ባህር ከሚገኙት የጦር መርከቦች በአንዱ ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት በተሳካ ሁኔታ ማክሸፍ መቻሉን አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን አስታውቀዋል።
የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃቱ የተሰነዘረው በየመን ሀውቲ ከተቆጣጠረው አካባቢ መሆኑንም ገልፀዋል።
በትናንትናው ዕለት በፈረንሳይ እንደራሴዎች ምክር ቤት ንግግር ያደረጉት የጦር ኃይሎች ሚኒስትር ሰባስቲያን ለኮርኑ ባለፈው ቅዳሜና እሁድ ስለከሸፈው ጥቃት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ለጥፋት የዘመቱት ሁሉም ጥቃት አድራሽ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ተመትተው መውደቃቸውን ተናግረዋል።
ከየመን የመጡት ሁለት ሰው አልባ አውሮፕላኖች በቀይ ባህር ላይ ቅኝት እያደረገች የነበረችውን ባለ ብዙ ተልዕኮ የፈረንሳይ የጦር መርከብ ኢላማ አድርገው እንደነበር አመላክተዋል።
እራስን ለመከላከልና ሁለቱን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ለመምታት የተወነጨፉት አስቴር 15 የተሰኙት ሚሳኤሎች መሆናቸውን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡
የተወሰደው እርምጃም በስኬት መጠናቀቁንና በዚህም መርከቧንና ሰራተኞችን መታደግ እንደተቻለ መግለፃቸውን አር ቲ ዘግቧል።
የየመኑ ሀውቲ አማፂ ቡድን በጋዛ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ለእስራኤል ይወግናል ብሎ ያመነውን ማንኛውንም መርከብ እንደሚመታ መግለጹ ይታወቃል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!