አንቶኒዮ ጉተሬዝ የኮፕ28 ተደራዳሪዎች ታዳሽ ያልሆኑ የኃይል አማራጮችን እንዲያስቆሙ አሳሰቡ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ኮፕ28 ታዳሽ ያልሆኑ የቅሬተ አካል ነዳጅን እንዲያስቆም አሳሰቡ፡፡
ዋና ፀሐፊው በዛሬው ዕለት በአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ28) የመጨረሻ ሰዓት ላይ ተደራዳሪዎች ‘ግትርነታቸውን’ ትተው የቅሬተ አካል ነዳጅን ማስቆም በሚቻልበት አግባብ ላይ ስምምነት እንዲደረስ አሳስበዋል፡፡
ጉተሬዝ ወደ ዱባይ የኮፕ28 የመሪዎች ጉባኤ መመለሳቸውን ተከትሎ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “አሁን ላይ ሁሉም የቅሪተ አካል ነዳጅን ማስወገድ አስፈላጊ መሆኑን መገንዘብ አለበት” ማለታቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።
ለኃይል ምንጭነት የሚያገለግሉት የተፈጥሮ ጋዝ፣ ድፍድፍ ነዳጅ እና የድንጋይ ከሰልን ጨምሮ ለአየር ንብረት መበከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።
ተመራማሪዎችም እነዚህም የኃይል ምንጮች እንደ ታዳሽ ኃይል ባሉ አማራጮች በመተካትና ዓለምን ከብክለት መጠበቅ እንደሚገባ ይገልጻሉ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!