Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አየር መንገዱ አቋርጦት የነበረው የማድሪድ በረራ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 28 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አቋርጦት የነበረውን የስፔን ማድሪድ በረራ አስጀመረ።

በረራው በፈረንጆቹ 2020 ተቋርጦ የነበረ ነው።

በዛሬው እለት የተጀመረው በረራ በሳምንት አራት ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን ስፔን ማድሪድን ከአፍሪካ እና ሌሎች አህጉራት ለማገናኘት ሚናው የጎላ ነው ተብሏል።

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው፣ የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ሀላፊ ለማ ያዴቻ፣ በኢትዮጵያ የስፔን አምባሳደር ማኑኤል ሳላዛር፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ስፔን የመጀመሪያ በረራውን ያደረገው በ1963 እንደሆነ ተገልጿል።

አየር መንገዱ የተለያዩ የተርሚናል ማስፋፊያ ስራዎችን እየሰራ መሆኑም ነው በመርሐ ግብሩ ላይ የተነገረው።

በፍቅርተ ከበደ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version