አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ-ህንድ ንግድ ልውውጥ በፕሬዚዳንት ፑቲን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ከተቀመጠው ግብ በላይ መሳካቱ ተገልጿል፡፡
በህንድ እና በሩሲያ መካከል ያለው ግንኙነት ውስብስብ የሆነ የጂኦፖለቲካዊ ከባቢ ቢኖርም እያደገ መምጣቱ ነው የተገለጸው።
ሰባት አስርት ዓመታትን ያስቆጠረው የዲፕሎማሲ እና የኢኮኖሚ ትብብር ጠንካራ መሆኑን የሁለቱም ሀገራት ባለስልጣናት በኒው ዴልሂ በተካሄደው የንግድ ኮንፈረንስ ላይ ተናግረዋል።
በህንድ የሩሲያ አምባሳደር ዴኒስ አሊፖቭ በህንድ የሚገኘው የሩሲያ የንግድ ተወካይ ጽህፈት ቤት 70ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ባከበረበት ወቅት እንደተናገሩት የሁለቱ ሀገራት አጋርነት እንደ ማዕቀብ እና ሁከትና ብጥብጥ ካሉ ዓለም አቀፍ አሉታዊ ተፅዕኖዎች የፀዳ ነው ብለዋል።
በሁለቱ ሀገራት መሪዎች በ2030 ለማሳካት የተነደፈውን የ50 ቢሊየን ዶላር በጥሩ ሁኔታ ማሳካት መቻሉንም ገልፀዋል፡፡
የንግድ ልውውጡ በዚህ ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ወደ 48 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር ማደጉን የገለፁት አምባሳደሩ፥ ከዚህ የበለጠ እያደገ እንደሚሄድም አመላክተዋል፡፡
በሁለቱ ሀገራት መካከልም ሳይታሰብ የመጣ ለውጥ እንደሌለ በንግግራቸው አረጋግጠዋል፡፡
የሩሲያ የኢንዱስትሪ እና ንግድ ሚኒስቴር ምክትል ኃላፊ አሌክሲ ግሩዝዴቭ የህንድን ኢኮኖሚያዊ እና ቴክኖሎጂ እድገት አድንቀዋል፡፡
ከአስርተ ዓመታት በፊት በሶቪየት- ከዛም በሩሲያ የተገነቡ ቴክኖሎጂዎች የህንድን የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት መሰረት ለመጣል ረድተዋል ማለታቸውን አር ቲ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!