Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

እስራዔል በጋዛ ለንጹሐን የደኅንነት ከለላ አልሰጠችም ስትል አሜሪካ ኮነነች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራዔል በደቡባዊ ጋዛ እየወሰደች ባለው እርምጃ ቃል እንደገባችው ለንጹሐን የደኅንነት ከለላ አልሠጠችም ስትል አሜሪካ በፅኑ ኮነነች፡፡

በጋዛ እየደረሰ ባለው የንጹሐን ዕልቂትም ዋሺንግተን እስራዔልን ኮንናለች።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጠንካራ ትችታቸውን እስራዔል ላይ ያሳረፉት በትናንትናው ዕለት የብሪታኒያ አቻቸውን ዴቪድ ካሜሩን በዋሺንግተን አግኝተው ካነጋገሩ በኋላ መሆኑን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

አንቶኒ ብሊንከን እስራዔል በደቡብ ጋዛ እርምጃ መውሰድ ከጀመረች ጀምሮ ለንጹሐን ጥበቃ አደርጋለሁ ብትል፥ መሬት ላይ እያየን ያለው ዕውነታ ግን በቃሏ እና በተግባሯ መካከል ልዩነት እንዳለ ነው ብለዋል፡፡

እስራዔል በበኩሏ በሃማስ ታጣቂዎች ጥቃት ከደረሰባት በኋላ ቡድኑን ሙሉ በሙሉ ጠራርጋ ለማጥፋት እየሠራች መሆኗን ገልጻለች፡፡

ሠላማዊ ዜጎችን ከጉዳት ለማዳን የተቻለውን ሁሉ እያደረኩ ነው ስትልም የቀረበባትን ወቀሳ ተከላክላለች።

እስካሁን ባለው መረጃ በጦርነቱ ከፍልስጤም ወገን 17 ሺህ 170 ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን 46 ሺህ ያኅል ደግሞ መቁሰላቸውን ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።

ከእስራዔል ደግሞ 1 ሺህ 200 ያኅል ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን ዘገባው አመላክቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version