የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ 100 ሺህ ችግኞችን ለጂቡቲ ላከች

By Alemayehu Geremew

December 08, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለሦስተኛ ጊዜ 100 ሺህ ችግኞች ለጂቡቲ መላኳ ተገለጸ፡፡

የድሬዳዋ አሥተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር እንዳሉት ኢትዮጵያ የጎረቤት ሀገራትንም አብሮ የማልማት ዕቅድ ይዛ ችግኞችን የማድረስ ሥራ በቀጣይነት እያከናወነች ነው።

በዚህም በድሬዳዋ አሥተዳደር በኩል ለጎረቤት ሀገር ጂቡቲ ለሦስተኛ ጊዜ 100 ሺህ ችግኞችን መላኳን ገልጸዋል፡፡

ዕቅዱ የተፈፀመው ቀደም ሲል በአጠቃላይ ለጂቡቲ 240 ሺህ ችግኞችን ለማድረስ ቃል በተገባው መሠረት መሆኑን የድሬዳዋ አሥተዳደር መረጃ ያመለክታል፡፡

መሠል ግንኙነቶች ጎረቤት ሀገራትን በልማት ከማስተሳሰር ባሻገር የባሕል የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ይበልጥ በማጠናከር መነቃቃት ይፈጥራል ሲሉም ከንቲባ ከድር ጁሀር አስረድተዋል ።