Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በመዲናዋ በበጀት ዓመቱ በቀን 70 ሺህ ሜ.ኩብ ውሃ ወደ ስርጭት ለማስገባት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በመዲናዋ በበጀት ዓመቱ በቀን ተጨማሪ 70 ሺህ ሜ.ኩብ ውሃ ወደ ስርጭት ለማስገባት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

ለዚህም በ1 ቢሊየን 457 ሚሊየን ብር በሚሆን ወጪ 42 ጉድጓዶች ቁፋሮ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።

በአሁን ሰዓት የ14 ጉድጓዶች ቁፋሮ ሥራ የተጠናቀቀ ሲሆን የ8 ጉድጓዶች ቁፋሮ በሂደት ላይ መሆኑ ተገልጿል።

የ6 ጉድጓዶች ቁፋሮ ሥራ ከጨረታው አሸናፊ ጋር ውለታ መገባቱ የተነገረ ሲሆን፤ የተቀሩት የ14 ጉድጓዶች ቁፋሮ ለማከናወን የሥራ ተቋራጭ ቅጥር በጨረታ ሂደት ላይ እንደሆነ ተጠቁሟል።

በበጀት አመቱ መጨረሻ ሁሉም ጉድጓዶች ተጠናቀው ወደ ስርጭት ሲገቡ አሁን ያለውን በቀን 792 ሺህ ሜትር ኪዩን ውሃ የማምረት አቅም ወደ 862 ሺህ ሜትር ኪዩብ ማሳደግ እንደሚቻል ከባለስልጣኑ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version