አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 14ኛው የወጣቶች ኮንፈረንስ “መጪውን ጊዜ በመገንባት ብልፅግናን ማረጋገጥ” በሚል መሪ ሐሳብ በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ነው።
የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ማቲዎስ ሰቦቃ እንዳሉት ወጣቱ ሀገሪቱን የሚገነባና ነፃነትን የሚያረጋግጥ የኢኮኖሚ ኃይል ነው ብለዋል።
የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ለወጣቶች እንቅፋት የሆኑትን ችግሮች በቅንጅት ለመፍታት እንደሚሰራም አስገንዝበዋል።
በአትሌቲክሱ ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት መሥራት እንደሚገባም ተናግረዋል።
ወጣቱ በሱስ ተጠምዶ የማይገባው ቦታ እንዳይውል ማዕከላት መገንባት እንዳለባቸው እና ችግሩ ከመሠረቱ ሊፈታ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ቢሮው ያለፉት አምስት ወራት የሥራ አፈጻጸሙን ከዞንና ወረዳ ከተውጣጡ ተሳታፊዎች ጋር እየገመገመ ነው።
በይስማው አደራው