Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፈረንጆቹ 2023 በታሪክ በጣም ሞቃታማው ዓመት ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንጆቹ 2023 በታሪክ ውስጥ በጣም ሞቃታማው ዓመት ነው ሲል የአውሮፓ የአየር ንብረት ለውጥ አገልግሎት ኮፐርኒከስ አስታውቋል፡፡
 
ክብረ ወሰኑን ለመስበር ሕዳር ወር ስድስተኛው ተከታታይ በጣም ሞቃታማው ወር የነበረ ሲሆን÷ አማካይ የቀን ሙቀት መጠኑም 14 ነጥብ 22 ዲግሪ ሴሊሺየስ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
በፈረንጆቹ 2020 ተመዝግቦ ከነበረው አንፃርም በ0 ነጥብ 32 ዲግሪ ሴሊሺየስ መብለጡም ነው የተገለጸው።
 
ለስድስት ወራት በተከታታይ እና ለሁለት ወቅቶች አዳዲስ ከፍተኛ የሙቀት መጠን መመዝገባቸውን የአገልግሎቱ ምክትል ዳይሬክተር ሳማንታ በርገስ ተናግረዋል፡፡
 
ይህ ያልተለመደውና በሕዳር ወር የተመዘገበው ከፍተኛ የሙቀት መጠን በ2023 ለየት ያሉ ክስተቶች መከሰት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ በጣም ሞቃታማው ዓመት ያደርገዋል ብለዋል።
 
በተጨማሪም በጥር እና ሕዳር መካከል ያለው አማካይ የሙቀት መጠን በቅድመ-ኢንዱስትሪ ጊዜ ከተመዘገበው አማካይ የሙቀት መጠን በ1 ነጥብ 46 ዲግሪ ሴሊሺየስ ከፍ ያለ እንደነበርም ተመላክቷል፡፡
 
እስካሁን በከፍተኛነቱ ከተመዘገበው የ2016ቱ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ደግሞ በ0 ነጥብ 13 ዲግሪ ከፍ ያለ እንደነበር ዘገባው አመላክቷል።
 
ኮፐርኒከስ አዲሱን ዘገባ ይፋ ያደረገው በዱባይ የሚገኙ ተደራዳሪዎች በኮፕ28 የመጀመሪያ ሳምንት ንግግራቸውን ለማጠቃለል በዝግጅት ላይ በነበሩበት ወቅት መሆኑን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል።
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version