Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከ50 ሺህ በላይ የባዮጋዝ ማብላያዎች አገልግሎት እየሰጡ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት አሥር ዓመታት በገጠሩ የኢትዮጵያ ክፍል ከ50 ሺህ በላይ የባዮ ጋዝ ማብላያዎች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ብሔራዊ የባዮጋዝ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ከኔዘርላንድ የልማት ድርጅት ጋር በመተባበር ባዮ ጋዝን ለገጠሩ የማኅበረሰብ ክፍል በማዳረስ ኑሮውን ማሻሻል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሚመክር መድረክ በአዲስ አበባ አዘጋጅተዋል፡፡

በመድረኩ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የገጠር ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ልማት መሪ ሥራ አሥፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ወልዱ÷ እስከ ፈረንጆቹ 2030 በሀገር አቀፍ ደረጃ የባዮጋዝ ማብላያዎቹን ቁጥር 165 ሺህ ለማድረስ መታቀዱን ገልጸዋል፡፡

ለገጠሩ ማኅበረሰብ የባዮጋዝ ማብላያ ተደራሽ ለማድረግ የሚያማክሩት አቶ መልካሙ ደሜ በበኩላቸው÷ ቴክኖሎጂው በዘጠኝ ክልሎች ውስጥ በ350 ወረዳዎች ለሚኖሩ አርሶ አደሮች ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

“ግሮውዝቲፕ ኮንሳልቲንግ” የተሠኘ በጉዳዩ ላይ የሚሠራ አማካሪ ድርጅት÷ ብድር ለማመቻቸት ከአበዳሪ ድርጅቶች ጋር መሥራት ያስችላል ያለውን ጥናት አቅርቦ ውይይት እንደተደረገበት ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በመድረኩ የክልል ውሃና ኢነርጂ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች፣ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት እንዲሁም የኦሮሚያና የአማራ ክልል የባዮጋዝ ማኅበራት ተሳትፈዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version