Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ስኳር ያላቸውን ምግቦች መመገብ ቢያቆሙ ምን ይፈጠራል?

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጤናማ የአመጋገብ ሥርዓት ስንከተል ከምግባችን ዝርዝር ውስጥ በመጀመሪያ ማውጣት የምንፈልገው ሥኳርንና የሥኳር ይዘት ያላቸውን ምግቦች ነው፡፡
በአንፃሩ ከሸንኮራ አገዳ ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ የምናገኛቸውን የተፈጥሮ የሥኳር ይዘቶች በመጠኑ መጠቀም ለጤና የጎላ ጥቅም እንዳላቸው የብራይት ሳይድ መረጃ ያመላክታል፡፡
ጥርት ያለ የፊት ቆዳ ፣ ጤናማ ጥርስ ፣ የተስተካከለ የነርቭ ሥርዓት እና የሰውነት ክብደት ከተፈጥሮ ከሚገኙ ስኳሮች የሚገኙ የጤና በረከቶች ናቸው፡፡
በመሆኑም በቀን የተመጠነ ተፈጥሯዊ የስኳር ይዘት መውሰድ እንደሚገባ የህክምና ባለሙያዎች ይመክራሉ።
አንድ ሰው ስኳር ሙሉ በሙሉ መጠቀም ቢያቆም ምን ይሆናል ? የሚል ጥያቄ በአዕምሯችን ሊከሰት ይችላል፡፡
1.  የፀጉር ዕድገት ይቀንሳል
ከሸንኮራ አገዳ ጭማቂ የሚገኝ የስኳር ይዘት ÷ የፀጉርን ውፍረት እና ዕድገት ከመጨመሩ ባሻገር ከሰውነት መርዛማ ንጥረ ነገሮችን እና ከመጠን ያለፈ የጨው መጠንን ለማስወገድ ብሎም የኩላሊትን ሥራ ለማቃለል ይረዳል፡፡
2.  የፊት ቆዳ በፀሐይና በዓየር ንብረት መለዋወጥ ይጎዳል
ከሸንኮራ አገዳ ጭማቂ ፣ ከጥቁር ቸኮሌት እንዲሁም ከአትክልት እና ፍራፍሬ የምናገኛቸው ስኳሮች የቆዳ ቀለም እንዳይጎዳ ፣ እንዳያረጅ እና ውብ ቀለም እንዲኖረው ይረዳሉ፡፡
3.  የሰውነት ክብደት ይጨምራል
ስኳር ባለመመገብ  የሰውነት ተፈጥሯዊ ፍላጎት አይቆምም ፤ ሥኳርን ይራባል ፤ እሱንም ለማሟላት ስኳር ካልተመገቡ ሰውነትዎ አብዝተው እንዲመገቡ ያስገድድዎታል በዚህም ክብደትዎ ይጨምራል፡፡
4.  የትኩረት ማጣት ያጋጥማል
በየቀኑ ሰውነትዎ መጠነኛ ስኳር ካላገኘ የትኩረት ማጣት ሊከሰትብዎ ይችላል ፤ በመሆኑም ጥቁር ቸኮሌት ቢመገቡ ወደ አዕምሮዎ የሚደርሰው የደም ዝውውር እንዲሻሻል ያስችላል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version