አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን በነገው ዕለት ወደ ተባበሩት አረብ ኤሚሬትስና ሳዑዲ አረቢያ በማቅናት የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገለጸ፡፡
ፕሬዚዳንት ፑቲን በሀገራቱ በሚኖራቸው የጉብኝት መርሐ -ግብር በተለያዩ የሁለትዮሽ ግንኙነቶቻቸው ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በተለይም ሀገራቱ በኢነርጂ ዘርፍ የነዳጅ ዘይት ላይ በትብብር መሥራት በሚችሉበት ሁኔታ እንደሚመክሩ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ድሚትሪ ፔስኮቭን ዋቢ አድርጎ ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
ፕሬዚዳንት ፑቲን በእስራዔልና ሃማስ መካከል የዘለቀው ግጭት በሚፈታበት መንገድ ከሀገራቱ ጋር እንደሚመክሩም ተመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!