ቻይና የአሜሪካ የባህር ኃይል መርከብ የውሀ ድንበሯን መጣሱን አስታወቀች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የባህር ኃይል መርከብ በህገ-ወጥ መንገድ የውሀ ድንበሯን ጥሶ ወደ ግዛቷ መግባቱን የቻይና መከላከያ አስታውቋል፡፡
የቻይና ወታደራዊ ኃይል በዛሬው ዕለት እንደገለጸው የአሜሪካ የባህር ኃይል መርከብ በህገ-ወጥ መንገድ ከሁለተኛው ቶማስ ሾል አጠገብ ካለው አወዛጋቢው የደቡብ ቻይና ባህር አቅራቢያ ገብቷል፡፡
የቻይና ደቡባዊ ወታደራዊ ተልዕኮ ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ አሜሪካ የደቡብ ቻይናን ባህር በማወክ የቻይናን ሉዓላዊነት ጥሳለች የቀጣናውን ሰላምና መረጋጋትም በእጅጉ አናግታለች ብለዋል።
ይሁን እንጂ የአሜሪካ የባህር ኃይል ተዋጊ መርከቡ በደቡብ ቻይና ባህር ውስጥ ከዓለም አቀፍ ህግ ጋር በተጣጣመ መልኩ መደበኛ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጿል።
የአሜሪካ የባህር ኃይል ባወጣው መግለጫ “በየቀኑ የ ዩ ኤስ 7ኛ መርከቦች በደቡብ ቻይና ባህር ውስጥ ለብዙ አሥርት ዓመታት እንዳደረጉት ሁሉ አሁንም ይቀዝፋሉ ብሏል።
እነዚህ ስራዎችም ነፃ እና ግልፅ የሆነ ኢንዶ-ፓሲፊክ ቀጣናን ለመጠበቅ ቁርጠኞች መሆናችንን ያሳያሉ ሲልም አክሏል።
ቻይና በደቡብ ቻይና ባህር ላይ ባለው ሰፊ የግዛት ይገባኛል ጥያቄ ከበርካታ ጎረቤቶቿ ጋር ውዝግብ ውስጥ መሆኗ ይነገራል።
በቅርብ ወራት ውስጥ ቻይና የፊሊፒንስ መርከቦችን ስታባርር እና የአሜሪካ መርከቦችም በ’አወዛጋቢው’ አካባቢ የሚያደርጉትን ጥበቃ ስትቃወም እንደነበር ሬውተርስ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!